ሪቻርድ ፋይንማን
Appearance
ሪቻርድ ፋይንማን (1910-1980) የ20ኛው ክፍለ ዘመን እውቅ የተፈጥሮ ህግጋት መርማሪ ነበር። የተወለደውም እዚያው አሜሪካ፣ ኩዊንስ እተባለ ከተማ፣ ኒው ዮርክ ክፍለ ሃገር ነበር። የመጀመሪያው የአቶሚክ ቦምብ ከሰሩት ሰዎች መካከል አንዱ ነበር። በራሱ በግሉ ባበረከታቸው የተለያዩ የጥናት ጽሑፎች ምክንያት የኖቤል ሽልማት አሸናፊም የነበር ሰው ነው።
ፋይንማን፣ የኳንተም ሜካኒክስን የእውቀት ዘርፍ ካዳበሩት ቀደምት ተማሪወች ወገን ነው። የመንገድ ማጎሪያ (ፓዝ ኤንቴግራል) ቀመርን ለኳንተም ሥነ እንቅስቃሴ በማዋሉና፣ የኳንተም ኤሌክትሮ-እንቅስቃሴ (ኤሌክትሮ ዳይናሚክስ)ን በማጥናቱ ስለዚህም ስራው ከሌሎች ሁለት ሳይንቲስቶች ጋር የኖቬል ሽልማት በ1957ዓ.ም. ተሸልሟል። የሂሳብ ቀመሮችንም አቅልሎ ለማሳየት የሚጠቅም የፋይናማን ምስል የተባለውን ዘዴም በመቀየሱ ስሙ ይጠራል፡፡
ፋይንማን፣ ከኳንትም ሜካኒክስ ውጭ የናኖ ቴክኖሎጂን፣ ኳንትም ስሌትን በመጀመር ይጠቀሳል። በተረፈም የመንኮራኩሯ ስፔስ ሸትል ቻሌንጀርን በአየር ላይ መጋየት ከመረመሩት ሰዎች አንዱ ነበር።
ከዚህ በተረፈ የሥነ ተፈጥሮ (ፊዚክስ) ትምህርትን ለሰፊው ህብረተሰብ ለማካፈል ባደረገው ጥረቱ ስሙ ይነሳል። ለዚህ ተግባሩ የደረሳቸው መጻህፍቱ ታዋቂዎች ነበሩ።
- About ስለ ሪቻርድ ፋይንማን
- ሊዮናርድ ሰሰኪንድ ስለጓድኛው ፋይንማን እንደመሰከረ
- ስለ20ኛው ክፍለ ዘመን ፊዚክስ እና ፊዚክስ አጥኝዎች ከታዋቂው ዩኒቨርስቲ (MIT) Archived ጁን 8, 2011 at the Wayback Machine