1952
Appearance
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1920ዎቹ 1930ዎቹ 1940ዎቹ - 1950ዎቹ - 1960ዎቹ 1970ዎቹ 1980ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1949 1950 1951 - 1952 - 1953 1954 1955 |
1952 አመተ ምኅረት
- መስከረም 4 ቀን - መጀመርያው ሰው ሰራሽ መንኮራኩር (የሩሲያ) ጨረቃን ደረሰ።
- ታኅሣሥ 22 ቀን - ካሜሩን ከፈረንሣይ ነጻነቷን አገኘች።
- ሚያዝያ 13 ቀን - የብራዚል ርዕሰ ከተማ ከሪዮ ዲዣኔሮ ወደ አዲሷ ብራዚሊያ ተዛወረ።
- ሚያዝያ 19 ቀን - ቶጎ ነጻነቱን ከፈረንሣይ አዋጀ።
- ሰኔ 13 ቀን - የማሊ ፌዴሬሽን (ዛሬ ማሊና ሴኔጋል) ከፈረንሣይ ነጻነቱን አገኘ።
- ሰኔ 19 ቀን - ማዳጋስካር ነጻነት ከፈረንሣይ አገኘች።
- ሰኔ 23 ቀን - ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ከበልጅግ ነጻነቱን አገኘ።
- ሰኔ 24 ቀን - ሶማሊያ ነጻነት አገኘ።
- ሐምሌ 25 ቀን - ቤኒን ከፈረንሳይ ነጻነት አገኘ።
- ሐምሌ 27 ቀን - ኒጄር ከፈረንሳይ ነጻነት አገኘ።
- ሐምሌ 29 ቀን - ቡርኪና ፋሶ "ላይኛ ቮልታ" ተብሎ ነጻነቱን ከፈረንሣይ አገኘ።
- ነሐሴ 1 ቀን - ኮት ዲቯር ነጻነት ከፈረንሣይ አገኘ።
- ነሐሴ 5 ቀን - ቻድ ከፈረንሣይ ነጻነቱን አገኘ።
- ነሐሴ 7 ቀን - የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ነጻነት ከፈረንሣይ አገኘ።
- ነሐሴ 9 ቀን - ኮንጎ ሪፑብሊክ ነጻነቱን ከፈረንሣይ አገኘ።
- ነሐሴ 11 ቀን - ጋቦን ነጻነት ከፈረንሣይ አገኘ።
- ነሐሴ 14 ቀን - ሴኔጋል ከማሊ ፌዴሬሽኑ ወጣች።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |