Jump to content

የቬትናም ጦርነት

ከውክፔዲያ
የቬትናም ጦርነት በ1957 ዓም

የቬትናም ጦርነት1948 ዓ.ም. እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ በቬትናም የነበረ ጦርነት ነበር።

ይህ ጦርነት እንደ ኮሪያ ጦርነት ሳይሆን ከተመድ ምንም በረከት ያላገኘ ሥራ ነበር። ከ1946 ዓም የጀኔቭ ጉባኤ በኋላ የፈረንሳይ ቅኝ አገር የነበረችው የፈረንሳይ ኢንዶቻይናላዎስካምቦዲያስሜን ቬትናምደቡብ ቬትናም ተከፋፈለች። በቅርቡ ግን ከስሜን ቬትናም (በሶቪዬት ሕብረትና በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ድጋፍ) እና ከደቡብ ቬትናም (በዩናይትድ እስቴትስ ድጋፍ) መካከል፣ ኹኔታው ወደ እርስ-በርስ ጦርነት መራ።

በአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ዘመን በየወገኑ የቻይና ወይም የአሜሪካ ሚለታሪ አማካሪዎች በቬትናም ተገኙ። ባጠቃላይ አሜሪካውያን ግን ስለ ቬትናም ባሕል ወይም ታሪክ ያወቁት እምባዛም ነበር።

በተለይ ኬኔዲ በጥይት ተገድሎ ምትኩ ፕሬዚዳንቱ ሊንደን ጆንሰንኅዳር 1956 ዓም ፕሬዚዳንት ከሆነ በኋላ፣ ��በብ አድርጎ ቬትናም ትልቅ የአሜሪካ ጦርነት እንዲሆን አሰበ። በነሐሴ ወር 1956 ዓም ስሜኑን በቦምብ መደብደብ ጀመረ፣ ይህ እስከ 1961 አም ድረስ ያለመቋረጥ ተቀጠለ። ከ1957 ዓም ጀምሮ ጆንሰን ብዙ የአሜሪካ ወጣት ልጆች ወደ ሥራዊት በግዴታ ምዝገባ አስገብቶ ወደ ቬትናም ጦርነት ይላኩ ነበር።

1960 ዓም ጀምሮ አሜሪካ በስሜን ቬትናም ላይ እንደማይሸንፍ ግልጽ ሆነ። በዚህም ሰዓት በአሜሪካዊ ሕዝብ አስተያየት ትልቅ ጸረ-ጦርነት እንቅስቃሴ ተነሣ። ነገር ግን የአሜሪካ መንግሥት ጦርነቱን አላስጨረሱም። ብዙ የማያስፈልግ መከራ ተደረገ። ከደቡብም ቬትናም ሕዝብ ግማሹ ስሜኑን ቬትናም ከአሜሪካውያን በላይ እንደ መረጡ ይመስል ነበር።

በ1961 ዓም በተደረገ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ የጆንሰን ዴሞክራት ወገን በጭራሽ ተሸነፈ። አዲሱ ፕሬዚዳንት ሪቻርድ ኒክሰን እንደ ቃሉ ወታደሮች ከቬትናም ማስወጣት ጀመረ። ይህ ግን እጅግ ቀስ ብሎ ተደረገ። በ1962 ዓም ደግሞ የአሜሪካና የደቡብ ቬትናም ኃያላት ወደ ካምቦዲያ ገብተው ወረሩ፤ ከዚህ አንሥቶ በአሜሪካ ትልቅ ተቃውሞች ተደረጉ።

በታህሳስ ወር 1965 ዓም ጦርነት ሳይጨርስ ኒክሰን ስሜኑ ቬትናም በፍጹም እንደ ምንጣፍ በቦምብ እንዲደበደብ አዘዘ። አሁን ለዚህ መልስ ተቃወሞቹ የተደረጉ በአለም ዙሪያና በተለይ በአውሮፓ ተደረጉ። በመጨረሻ የምዕራብ ጀርመን ፕሬዚዳንት ቪሊ ብራንት ለኒክሰን ተናግሮ መደብደቡን አሁን ካልጨረስክ የአውሮፓ ግንኙነቶችህ በአደጋ ውስጥ ገብተው ነበር ብሎ አሳመነው።[1] መደብደቡም በዚያች ቀን ተወ፤ በአንድ ወርም ውስጥ የአሜሪካ ሥራዊት በሙሉ ከቬትናም ወጡ።

ከዚህ በኋላ እርስ-በርስ ጦርነት ከስሜንና ደቡብ መካከል እስከ 1967 ዓም ድረስ የስሜኑ ኃያላት ሳይጎንን እስከያዙ ድረስ ተቀጠለ፤ ከ1967 ዓም ጀምሮ አንድ የተዋሀደ አገር ቬትናም ሆኗል።

  1. ^ Edward W. Knappman, ed. South Vietnam: Volume 7, US-Communist Confrontation in Southeast Asia 1972–1973. p. 226.