Jump to content

ኤሽኑና

ከውክፔዲያ
ኤሽኑና
(ተል አስማር)
የሚጸልይ ምስል፣ ኤሽኑና
ሥፍራ
ኤሽኑና is located in መስጴጦምያ
{{{alt}}}
መንግሥት አካድ፣ ኤላም፣ ዑር፣ ኢሲን፣ ላርሳ፣ ባቢሎኒያ ወዘተ.
ዘመን 2075-1674 ዓክልበ. ግድም
ዘመናዊ አገር ኢራቅ
ጥንታዊ አገር ሱመር

ኤሽኑናሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው ተል አስማር ተብሎ በዘመናዊው አገር ኢራቅ ውስጥ በዲያላ ወንዝ ሸለቆ ይገኛል። ኤሽኑና ከስሜኑ ተራሮች ወደ መስጴጦምያ በደረሰው መንገድ ላይ ስለተቀመጠ የብርቅ ሸቀጦች (ፈረስሰንፔር፣ ዕንቁዎች ወዘተ.) ንግድ ማዕከል ሆነና በለጸገ።

አካድ መንግሥት እየደከመ (በሹዱሩል ዘመን 2001-1986 ዓክልበ. ግ.) ኤሽኑና በአካድ ቅሬታ ግዛት ውስጥ እንደ ቀረ ይታወቃል። ከዚያ የኤላም ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ያዘው። ከዚህ በኋላ ለዑር መንግሥት ተገዥ ሆነ፤ ከዚያ በተራው ለኢሲንና ለላርሳ ተገዛ። አንዳንድ የኤሽኑና ገዢ ግን እንደ ነጻ ንጉሥ ይገዛ ነበር። 2 ኢፒቅ-አዳድ 1771-1729 ዓክልበ. በተለይ ለኤሽኑና ሰፊ ግዛት አሸነፈ። በመጨረሻ በ1674 ዓክልበ. ኤሽኑና ለባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ወደቀ።

የኤሽኑና ሕግጋት ደግሞ ለሥነ ቅርስ ታውቀዋል፤ የትኛው ንጉሥ እንዳወጣቸው ግን እርግጥኛ አይደለም።

የኤሽኑና ነገሥታት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

(ኡልትራ አጭር)

የኤሽኑና መንግሥት በ1680 ዓክልበ.