ቆምጬ አምባው
ይህ መጣጥፍ ከተመሳሳዩ መጣጥፍ ከቆምጬ ኣምብው ጋራ እንዲዋሐድ የሚል ሀሣብ ቀርቧል። (ውይይት) |
ቆምጨ አምባው የጎጃም ክፍለ ሀገር የአንድ ወረዳ ገዢ ነበሩ ። ቆምጬ አስተዳዳሪ ሳሉ የአንበሳ ሰል አሰርተው ከግርጌው «ጎጃም አንበሳ ነው» የሚል ጽሁፍ አሰፈሩበት ። ህዝቡም በዚህ ተደስቶ ሲኖር ሳለ ገበሬው ግብር በጊዜ አላስገባ ብሎ አስቸገራቸው ። ይህእኔ ቆምጬ ገበሬውን ሰብስበው «አሁን ይሄን አምበሳ ላም ላድርገው ?» በማለት ግዳጁን እንዲወጣ አደረጉት ይባላል ። አዎን፣ በቆምጬ ስም የሚነገሩ በርካታ ቀልዶች አሉ ። ያለማጋነን ቆምጬ የዘመነ ደርግ አለቃ ገብረሀና ነበሩ ። እርሳቸው ግን ይሄንን ክብር በመቀዳጀታቸው ደስተኛ አይደሉም ።
"ብቻ የትም ቦታ በምሄድበት ጊዜ ሰዎች የጠቆአቆሙብኛል ። በብዛት ዞረው ያዩኛል ። እኔ ሰዎቹን አላውቃቸውም ። አሁን በሄ ሰሞን እንክዋ (1985) አዲስ አበባ ሄጄ ነበር ። ቅድም እንዳልኩህ ልጄን ጠይቄ ነው የመጣሁኝ ። እዚያ አንድ ለቅሶ ነበር ። እዚያው ነው ደርሼ የመጣሁኝ ። እና ታድያ ያው እዚያ ያው እዚያ .. ይሉኛል ። እንዴ ? አልሰረቅኩ : አልቀጠፍኩ ። እኔ ከሰው የተለየ ስራ አልሰራሁ ። ...እና ይሄ ሁሉ እኮ ሰው ያወጣልኝ ስም ነው ።" ስለ ቆምጬ ሲነሳ አያሌ ቀልዶች ትዝ ይሉናል ። እኒያ በቆምጬ አምባው ስም የሚነገሩት ቀልዶችና የግለሰቡን ህይወት የተመለከተ ቃል ምልልስ አዋህጄ እንዲህ አቅርቤዋለሁ ። "ትክክለኛ ስሞ ማን ይባላል ?" "ቆምጬ አምባው ይልማ ፤ እንደዚያ ነው የምባለው ።" "የህይወት ታሪክዎን ባጭሩ ቢነግሩኝ " "በ1933 ጎዛምን ወረዳ ውስጥ ማያ አንገታም ቀበሌ ነው የተወለድኩት ። ከዚያ ለትምህርት እንደደረስኩኝ እናትና አባቴ ቤተ እየሱስ የተባለ ትምህርት ቤት አስገቡኝ ። ከዚያም ዳዊትና ድጉአ ጽሞ ድጉዋ ወጥቼ ደብረ ኤልያስ ቅኔ ትምህርት ቤት ገባሁኝ ። እዚያ እንደገባሁ በችታ ገባ ። አባቴ ከዚያ አውጥቶ አገሬ መልሶ ወሰደኝ ፤ አያይ በሽታው ይበርዳል መልሰህ እዚያው ጨምረኝ ብለው አባቴ እምቢ አለኝ ። ከዛ እዚያው ደብረ ኤልያስ ትምህርት ቤት ገባሁና የስድስተኛ ክፍል ትምህርቴን አጠናቀቅኩ ። ከዚያም የነበረው ባህል መሰረት በልጅነቴ ጋብቻ መሰረትኩ ። አሁን የአስር ልጆች አባት ነኝ ። ከዚያ የናት ያባቴን ከብቶች ገንዲ የሚባል በሽታ ገብቶ ስለፈጃቸው በ1958 ወህኒ ፖሊስ በወታደርነት ተቀጠርኩ ። የ10 አለቅነት ማእረጌን እንደያዝኩ በ1971 የወረዳ አስተዳዳሪ ሆኜ ተሾምኩ ።"
"እስከ 6ተኛ ክፍል ብቻ ነው የተማሩት ?"
"በወረዳ አስተዳዳሪነት ከቢቡኝ ደብረወርቅ እንደተዛወርኩኝ ከ7ተኛ - ዘጠነኛ ክፍል ትምህርቴን ፈጽሜ በተለኮ (በኮርስፓንዳንስ ) 12ኛ ክፍል ትምህርቴን አጠናቅቄያለሁ ።"
"የት የት ቦታ ሰርተዋል ?" "ቢሆን : እነሴ : እናርጅ እናውጋ : አቸፈር : ማቻከል : ወረዳዎች በወረዳ አስተዳዳሪነት ሰርቻለሁ ።" "የሰሩዋቸው ስራዎች ምን ምን ናቸው ?" "እንግዲህ እኔ በተዘዋወርኩበት ወረዳ ሁሉ ትምህርት ቤቶች : የጤና ማህበራዊ መገልገያዎች : መንገዶች : ንጹህ የመጠጥ ውሀ ያልሰራሁበትና ያልመሰረትኩበት የለም ። በተለያዩ ወረዳዎች ከ20 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከ10 ያላነሱ ኪሊኒኮች 1 የጤና ጣብያ ሰርቻለሁ ። የተለያዩ የስፖርት ማዘውተርያ ስፍራዎችንም ሰርቻለሁ ። በዚህ መስክ ለምሳሌ በሞጣ ዙርያ አንድ ከፍተኛ የስፖርት ሜዳ አዘጋጅቼ በ1977 የኢትዮጵያ ትቅደም ዋንጫ ውድድር እንዲደረግበት አድርጌያለሁ ። ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ብሄራዊ ዘመቻዎች ባለትም በመሰረተ ትምህርት ዘመቻ በተለያየ የጤና ነክ ዘመቻዎች በክትባትና በመሳሰሉት ህዝቡን በማንቀሳቀስ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ሳይቀር ሽልማትና እርዳታ አግኝተናል ። በነዚህ ህዝቡን አስተባብሮ ግብር የሚያስገባ ካለ ይህንኑ መሳርያ ያገኛል ብዬ አስነግራለሁ ። ታድያ ሁሉም ባንድ ጊዜ አስገብቶ ያንን መሳርያ ለማግኘት ገበሬውን ለምኖና ቢሆን እባክህ ቶሎ አምጣ እነ ልሸለምበት እያለ በማስተባበር ያንን የዘመኑን ግብር ወድያው ያስገባል ። እና መሳርያ እንጨት ነው ምን ችግር አለ ። ሌላ ነገር የምርምር መሳርያ እንደዚህ መስጠት ነው እንጂ እማያቅተን ሰው እሚያጠፋ ነገር መስጠት ምን ይቸግረናል ። ያንን እያነሳን እንሸልመዋለን ።"
"እሱማ ዋናው ነው እንጂ ። የኔ ዋናው ማበረታቻ እሱ ነው ። በቀጥታ የተሰራውን ስራ ወስጄ በሬድዮና በጋዜጣ አስነግርለታለሁ ። ያንን ጋዜጣ ደግሞ በባህር ዳር ወይም ደብረ ማርቆስ በመውጣት ቶሎ አምጥቼ እየው እንዲህ ያለ ስራ ብትሰሩ ስማችሁ በጋዜጣ ይወጣል ብየ ያንን ጋዜጣ ወስጄ ቢሯቸው ላይ እለጥፍላቸዋለሁ ። ያነ የገለ ስም በሬድዮ ተጠርቶ በጋዜጣ ወትቶ የኔ ቀበለ ሊቀር ነው ወይ ? እያለ እሚቆጭ ይበዛል ። እንዲያውም የኛ አይነገርም ባዩ እየበዛ ስለመጣ የሰራኸውን አይቼ ትክክለኛ ሆኖ ካገኘሁት ይተላለፍልሀል እምላቸው ብዙ ነበሩ ።
"የርሶ ስም ብዙ ጊዜ በሬድዮ ይተላለፋል ?"
"አዎ ፤ እንዲያውም ማስታወቅያ ሚኒስቴር የቆምጬ አምባው ነው ። ሁልጊዜ የሚነገረው የሱ ነው ። እሱ ገዝቷቸዋል ። ጋዜጠኞች ሲሄዱ ይጋብዛቸዋል ። ቢራ ያጠጣቸዋል ። መስተንግዶው ከባድ ነው እያሉ ይሰድቧቸዋል ። ይህንን ግን የሚያስወሩብን እንደኔ ያልሆኑ መስራት የተሳናቸው ሁላ ናቸው ። ታድያ እነሱም የት አለ ስራ ? የሰራችሁትን አሳዩንና እናስተላልፍላችሁ ሲሏቸው ምናም ዘመቻዎችም ሆነ ግብር በማሰባሰብ ሂደት የተስተካከለኝ አልነበረም ። አንደኛ ነው ሁልጊዜ የምወጣው ።"
"እነዚህን ሁሉ ስራዎች ሲያከናውኑ ህብረተሰቡን ለማግባባት የሚጠቀሙበት ዘዴ ምንድነው ?"
"እንግዲህ አንደኛ የበለጠ ውጤት ለማግኘት አርሶ አደሩን አለመለያየት ነው ። ሁለተኛ ደግሞ በየጊዜው ማስተማር መቀስቀስ ነው ። አብዛኛውን በማያመርትበት ቀን ስራ በማይሰራበት ቀን ሁሉም ሀላፊ ተበትኖ እሱ ዘንድ እንዲሄድ ስለምፈልግ ሁላችንም እንሄዳለን ። በዝያ በረፍት ቀን ለምን ቤተክርስቲያን አይሆንም እንዲያው እዚያ ጥሩ ነው ። ሰው አዳራሹ ተኮፍሶ ንግግር የሚጥም አይመስለውም ፤ ደሞ ሰው ሙቶም ከሆነ ባንድ በኩል ለቅሶው አያለ ባንድ በኩል ስለትምህርት ብናስተምረው ገለጻ ብናደርግለት ይሰማል ። ለላው ያው ሽልማት ማበረታቻ መስጠት ነው ።"
"በችልማት ማበረታቻ ሲሉ እንዴት ነው ? ምን ምንድነው የሚሸልሙት ?"
"ለም��ሌ እኔ አንድ ዝግጅት ወይም ስብሰባ እንደዚህ አዘጋጅና ደካማ የሆነውን ሊቀመንበር መጨረሻው ወንበር ላይ እንዲቀመት ነው የማደርገው ። በጣም ጎበዝ ኮከብ የሆነውን ደግሞ ግንባር ላይ ነው እማስቀምጠው ። ግብር እሚያስገባ በጸረ ስድስት ክትባት ጥሩ ውጤት ያሳየውን «ና ያንተ ወንበር ይሄ ነው» ብዬ ከፊት አስቀምጠዋለሁ ። እንደሱ ለመቀመጥ ሲል ሌላው የግድ ይሰራል ። ሌላ ደግሞ ለምሳሌ ግብር በደንብ አድርጎ ለማስገባት እነ የማሰር የማስገደድ ስልት አልጠቀምም ። ይሄ ምንድነው ተመንጃ እሱን አስመጣና 3ስቱን አንድ ላይ በማዋቀር አውላላ ሜዳ ላይ አቆመዋለሁ ። እና ቶሎ የሰሩት የላቸውም ።"
"ሬድዮ ሲሉ ትዝ አለኝ ይሄስ ምንድነው አንድ ቀን እርስዎ አውቶቡስ ውስት ሆነው ወደክፍለሀገር በመጉዋዝ ላይ እያሉ እንደአጋጣሚ የዜና ሰአት ነበርና ዘና ሲወራ የእርስዎ ስም በመጠራቱ ሹፌሩን አቁም አቁም በማለት ወደመንገደኞቹ በመዞር ስሙ ስሙ ቆምጬ አምባው ማለት እኔ ነኝ በማለት ....?"
"ይሄ ሀሰት ነው ። ጨርሶ ካንደበተ አልወጣም ። ለማንኛውም ጥያቄው በመቅረቡ ደስ ነው ያለኝ ። ይሄ ሊወራብኝ የቻለው እንዴት መሰለህ ? ገና የወረዳ አስተዳዳሪ ሆኜ ቢሆን እንደሄድኩኝ አንድም ወፍጮ በወረዳው አልነበረም ። እና ደካሞች እርጉዞችሰቶች ድንጋይ ከድንጋይ እያፋጩ ፍዳ ያዩ ነበር ። ስለዚህ ህዝቡን አስተባበርኩና 15 ሺ ብር እንዲያዋጣ አድርጌ ወፍጮ ቤት አስተከልኩ ። እና ያ ወፍጮ ተገዝቶ ስራ ሲጀምር በሞጣ የሚገኘው ወፍጮ ስራ ጀመረ ተብሎ በሬድዮ ተነገረ ። እና በስራና በልማት የቀደምኩዋቸው አስተዳዳሪዎች ያንን አስወሩብኝ ።"
"ምን ብለው ነው ያስወሩብዎት ?"
"እንደው ዝም ብለው ስራ ሳይሰሩ እየተንጠራሩ ወደ ህዋላ ይቀሩና እኔ በልማት የቀደምኩዋቸው ምን ይላሉ «ወፍጮ ስራ ጀመረ» ተብሎ በሬድዮ ሲነገር ቆምጬ አባይ ላይ ነበር ። ከአዲሳባ ወደጎጃም ይመጣ ነበር ። እና እኔ ነኝ ቆምጬ አምባው እወቁኝ ብሎ በአውቶብሱ ላይ ተናገረ ብለው ይህንን አስወሩ ። ያስወሩ ። እሚያሸንፍ ተግባርና ስራ ነው ። ሌላ ማንም ቢያወራ አይለጠፍብኝም ። የህዝቡ ማህበራዊ ችግር ግን ካለችኝ ጭላንጭል እውቀት ጋር ከዚያ ህዝብ ጋር በማገናኘት ችግሩን ልፈታለት ሞክሬያለሁ ። እንዴ ወፍጮውን እኮ እንዲያ ሳስተክለው ህዝቡ «የታለ ያ ወፍጮ እሚፈጨው ሰውዬ» እያሉ ወፍጮ አይቶ ስለማያውቅ «ለመሆኑ ምን ይመስላል ምን አይነት ሰው ነው» እስከማለት ደርሶ ነበር እኮ ።"
"ደሞ ለሎች አሉ ። በርሶ ስም የሚነገሩ ቀልዶች እንደዚህ ። ስለነሱ እሚያውቁት ነገር አለ ?"
"እንግዲህ እንዲህ ያለ ጥያቄ ተዚህ ቀደም ቀርቦልኝ አንድም ቀልድ እንዳልቀለድኩ ተናግሬያለሁ ። እኔ ስራ እንጂ ቀልድ አልወድም ። ለቀልድ ጊዘ አልነበረኝም ። እንዴው በየጊዘው አሁን ድረስ እዚህ እየመጡ እሚያስቸግሩኝ አሉ ። ከተለያዩ መጽሄቶች እንደዚህ መጣን እያሉ ይጠይቁኛል ። አንዳንዶቹ እንደው ባንተ ስም መጽሀፍ ልንጽፍ ፈልገን ነበር ። ወድያውም ታሪክ ነው እያሉ ይጠይቁኛል ። እኔ ግን ወይዱ እኔ የናንተ መጽሄት ማሻሻጫና ማዳመቅያ አይደለሁም ደሞም ያላልኩትን ብትሉ እከሳለሁ እያልኩ ብዙዎቹን መልሻለሁ ።
"ታድያ እነዚህ ቀልዶች ከምን የመነጩ ይመስልዎታል ?"
"እንግዲህ በምሳለ ልንገርህ ። ለምሳሌ እንደዚህ እንደዝያ አስወሩብኝ ። የክፍለ ሀገሩ ፓርቲ ኮሚተ ተሰብስቦ «በቀጥታ ወደሶሻሊዝም መግባት ሲቻል የብሄራዊ ዲሞክራሲ አብዮት ፕሮግራም ለምን አስፈለገ ?» በማለት ቆምጬን ጠየቀው ። ታድያ ቆምጨም «እንዴ ! ታድያ ሶሻሊዝምን በቀጥታ አታደርጉትም ? ባለስልጣኖቹ እናንተው አይደላችሁ ? ቆምጬ ከለከላችሁ ታድያ ?» ብሎ መለሰላቸው በማለት አስወሩብኝ ። እንግዲህ ይህ ምንን ያመለክታል ? እኔ ደካማ አላዋቂ መሆኔን በማሳየት ምንም አይነት የልማት ስራ መስራት እንደማልችል ለማሳየት ከማሰብ የመነጨ ነው ።"
"ለምሳለ ቀድሞ በሞጣ አካባቢ አንድ ትልቅ የስፖርት ሜዳ ማሰራትዎን ገልጸውልኛል ። እና ያንን ሜዳ መርቀው ሲከፍቱ «እንግዲህ ይህን ሜዳ የምንጠቀመው በቁጠባና በእቅድ ነው ፤ በይህ መሰረት በጋ በጋ ትጫወቱበታላችሁ ። ክረምት ክረምት ደግሞ ይታረሳል .....» ብለዋል እሚባል ነገር አለ ። እና ...?"
"ደግሞ እንዲህ አሉ ? ይበሉ ምናለ ። እኔ ግን ካንደበቴ አለመውጣቱን ነው እማውቀው ። ደሞ ይሄኛውን አልሰማሁትም ። እኔ የሰማሁት ሌላኛውን ነው ።"
"ምንድነው የሰሙት ?" "አዎ አንደዜ ቆምጬ የስፖርት ሜዳ ሲሰራ ... እንግዲህ ያነ ሜዳው ሲሰራ ይህእ ሩል መንገድ ይጠቀጥቅ ነበር ...እና እኔም ቱታ ለብሼ ያንን መንገድ እጠቀጥቅ ነበር ። እና ምናሉ ካሳዬ አራጋው ያነ ወደሞጣ ይሄዱ ነበርና እግረ መንገዳቸውን ቆምጬን አንደ ላናግረው ብለው ና ብለው ቢጠሩት ያንን የስፖርት ሜዳ እየሰራ "አይይ እኔ አልመጣም አብዮት የማያቁዋርጥ እንቅስቃሴ ነው ። እና እኔም በአብዮታዊ ስራ እንቅስቃሴ ላይ ስለሆንኩ አቁዋርጬ አልመጣም" ብሏቸው እምቢ ብሎ ቀረ ...እያሉ አስወሩብኝ ። እና ይህእ ምንን ያሳያል ? ማእከላዊነት አለመጠበቅ ብልግናን የሚያሳይ ነው ። ግን እውነቱ እሳቸው አልመጡም ። እኔም እንዲያ አላልኩም ።"
"ፖለቲካ ትምህርት በት ገብተው ነበር ?"
"አዎ ገብቻለሁ ። አዎ ደሞም ከዚያ አንድ ቀልድ ነበረች ። ያነ እምፔርያሊዝም የሚባል ነገር ነበርና አንዱ ተነስቶ ክፍል ውስት ሲያወራ "ብዚ አገሮች ከቅኝ አገዛዝ ነጻ በመውጣታቸው እምፐርያሊዝም እርቃኑን ቀርቷል ..." ብሎ አለ ። እና ቆምጨም ብድግ ብሎ "ቁጭ በል አንተ ውሸታም ። እምፔርያሊዝም እርቃኑን ሲሆን ሽንት ቤት ነው ወይ ቆሞ ያየኽው ? የታባክ ነው ያየኸውን ነው የምታወራው ?" ብሎ ተናገረ እያሉ አውርተውብኛል ። እኔ ግን አላልኩም ።
""ግን የፖለቲካ ትምህርት ቤት ህይወትዎ እንዴት ነበር ? ይሄው አሁን እንኩዋን ከበተክስያን ነው የመጡት ። ሀይማኖትና ማለን እንዴት ያስከዱት ነበር ?"
"አዎ እኔ መንፈሳዊነተ መቼም ቢሆን አይለየኝም ። በዚህም የተነሳ ፖለቲካ ትምህርት ቤት ውስት እየጸለየ ዳዊት ተያዘበት ብለው አስወርተዋል ። እርግጥ ግን እግዜርን መቼም ልበ አልካደውም ። ደሞም እዚያ ስገባ ማርኪሲዝም ሌኒኒዝም ያራምዳል ብለው ሳይሆን በትምህርት ቢታገዝ ህብረተሰቡን አስተባብሮ ልማትን ሊያፋትን ይችላል ብለው ነው ። በተረፈ ፖለቲካ ትምህርት በት ውስት ትዝ የሚለኝ አንድ ጊዜ ተከስሼ ነበር ። ትምህርት ቤቱ አካባቢ የሆነ ቡድን የልማት አስተባባሪ አድርገውኝ ነበር ። እና እነ ልማትና ስራ የለመድኩ ስለሆነ ካድሬዎቹ ለዘራቸውን ወርቃቸውን አድርገው ሲንጎራደዱ እነ ቱታ ለብቼ እሰራ ነበር ። እና ውሀ እጠልፋለሁ ። ድንጋይ እፈነቅላለሁ ። ምን እላለሁ ። እና ባንደዘ ሶስት ሜዳ ቆፍረ ጨረስኩ ። ይህእንን ያዩ ካድሬዎች ኡኡ ብለው ከሰሱኝ ። ገበሬውን አምጥታችሁብን በቁፋሮ ፈጀን ብለው አመለከቱብኝ ። አንሰራም ብለው አመጹ ። እና እኔም አልሰራ ካሉ ይቅር እንጂ የምን ክስ የምን ጣጣ ነው ብየ ተከራከርኩ ። ህዋላ ከሰራችሁ ስሩ ተብለው በነሱ ተፈረደ ። እንግዲህ የማስታውሰው ይሄን ይህእን ነው ።"
"ከቀድሞ ባለስልጣናት ጋር የነበረዎት ግንኙነት ምን ይመስል ነበር ? ከፕሬዚዳንት መንግስቱ ጋርስ ተገናኝተው ያውቃሉ ?"
"ከፕሬዚዳንቱ ጋ የሚያገናኘኝ ነገር የለም ። እነ አግኝቻቸውም አላውቅ ። ግን እኔ ያልተናገርኩትን ነገር እየተናገሩ ብዙ ነገር ተወርቷል ። እና እነም እሰጋ ነበር ። ግን የደረሰብኝ ነገር የለም ። ለምሳለ አንደዜ ምናሉ ባንድ ወቅት ሊቢያና ቻድ ተጣልተው ነበር ። እና ያነ ደሞ የወቅቱ የአፍሪካ ሊቀመንበር ፕሬዚዳንት መንግስቱ ነበሩ ። እና ካሳየ አራጋው ቆምጬን ጠርተው "ቆምጬ አንተ ጎበዝ ነህ እና ባንተ አስተያየት የሊቢያና የቻድ ግጭት ምን ይመስልሀል ?" ብለው ጠየቁትና ቆምጨም ..."እንዴ እኔን ምን ትጠይቁኛላችሁ ሊወመንበር መንግስቱ ያልቻሉትን ሂጀ ላስታርቅላችሁ ነው ወይ ..?" አለ ብለው አስወሩብኝ ። እና በለላ በኩል ደግሞ እነ ከባለስልጣናት ጋር ግንኙነት የለኝም ። እንዴውም ያን ያህል ስደክም ለአውራጃ አስተዳዳሪነት ስሾም ስመን በፍሉድ አጥፍተው ለላ ሰው ሹመውበታል ::"
"እንዴው ምንም ቀልድ ወጥቶኝም አያውቅም ነው ሚሉት ?"
"እኔ በጭራሽ ። እርግጥ ምንድነው እነ ያልኩትን በሌላ እያዞሩ እሚያወሩት ነገር አለ ። እነን ለማጣላት ። ለምሳሌ አንደዜ ከደብረኤልያስ ድርጃ ገብረኤል እሚባል አገር ከአንድ ዋና አስተዳዳሪ ጋር እየሄድን ነበር ። በመኪና ነበር እምንሄድ ። እሳቸው የእህል ኮታ ሊገመግሙ ነው የመጡት ። እኔ ደሞ የመሰረተ ትምህርት የምስክር ወረቀት ልሰት ነው ። እና ስንሄድ ከፊታችን 3 አህዮች እየጋለቡ ይሄዳሉ ። ይሄነዜ አስተዳዳሪው ወደነ ዞር አሉና "ቆምጬ እነዚህ አህዮች ምንድናቸው ? ከቅድም ጀምሮ ከፊት ከፊታችን ይጋልባሉ ? "ብለው ጠየቁኝ ። እና እነም "እየውልዎ እንግዲህ እርሶ በደንብ አድርገው የሚገመግሙ ከሆነ እነ ሀገር እንኩዋን ሰው ይኸው አህያውም ነቅቷል ። እናም አቀባበል መሆኑ ነው "ብዬ አልኩአቸው ። እና ይቺን ወስደው አስተዳዳሪውን "አህያ ስለሆንክ አቀባበል እሚያደርግልህ አህያ ነው "አለ ብለው ዞር አደረጉአት ።"
"ሌባ አይወዱም ይባላል ለመሆኑ እንዴት እንዴት አድርገው ነበር ለባን የሚቀቱት ?"
"አዎ ለባ አልወድም ። አንደዘ ቢሆን ወረዳ እያለሁ ለባ በጣም በዛብኝ ። ይሰርቃሉ የተባሉትን ሁሉ ጠራሁና ጠበንጃ እያሸከምኩ ሾምኩአቸው ። በሉ እንግዲህ ጠብቁ አልኩና ሁለት ሁለት ካርታ ጥይት ሰጠሁዋቸው ። እናንተ ታጠፋላችሁ ተብሎ በሚስጥር ተነግሮኛልና አሁን እስቲ የሚያጠፋውን እናያለን ። እናንተ ግን ጠብቁ ብየ አደራ አልኩዋቸው ። ከዝያ ከብት አይሰረቅ ። ምን አይሰረቅ ሌባ ቀጥ አለ ። ታድያልህ ቆየት ብሎ አንደዘ ልበ ጠረጠረና ጋበዝኩዋቸውና አረቄ እየጠጣን "አይ " የናንተ ነገር አሁንም ትሰርቃላችሁ አሉ "ምነው እየለመንኩዋችሁ ? መሳርያ መግፈፍ ማሰሩ አይረባም ያጣላል ። ስለዚህ እባካችሁ ?" አልኩዋቸው ። በዚህ ጊዘ አንዱ ሞቅ ብሎት ነበርና "አይይ አያ ቆምጬ እኛኮ አንሰርቅም ። ብንሰርቅም ከርሶ አገር አይደለም ከዳሞት (ዋኖስ ...ቅቅቅቅ ) ነው "አለና አረፈው ። እና እኔም አለመተዋቸውን አወቅሁ ። እና እንዲያ እያደረኩ ነው ለባ የምይዘው ። ከማባረር ከማሰር እንዲህ ቀርቦ እያጫወቱ መያዝና መክሮ መመለሱን እመርጣለሁ ።""
"ብዙ ጊዜ እንዲህ እንዲህ ገጠር ውስጥ ተዘዋውረው ሲሰሩ መቸም አስተዳዳሪ ነዎትና የቢሮዎን ስራ ምን ጊዘ ነው የሚሰሩት ? ደሞ ስብሰባ ወደላይም ወደታችም ሊኖርብዎት ይችላል ?"
"እኔ ብዙ ጊዘ የቢሮ ስራ አልወድም ። 10 ቀን ቢሮ ካለሁ 20 ቀን እዳሪ ነኝ ። ስብሰባ እንኩዋን ስጠራ አልመጣም እያልኩ ብዙ ጊዜ እቃወማለሁ ። ዛሬ ተሰብስበን ነገ ስብሰባ ይሉኛል ። እነ ስንት የገጠር ስራ አለብኝ ፤ ከተቻለኝ አስፈቅዳለሁ ። ካልሆነም እምትወያዩበትን አጀንዳ በስልክ ንገሩኝ እያልኩ እጠይቃለሁ ። እና ያኔ "ስለ እህል ኮታ ስለትምህርት ስለምናምን ድክመት ነው ...." ይሉኛል ፤ አይይ እኔጋ ደህና ነው ፡ የደከመውን ጠይቁ ፤ ከደከመው ጋር ተሰባሰቡ እያልኩ ወደስራዬ እህእዳለሁ ::"
1. የመፈክር ጋጋታ የበዛበት ሰሞን ነው ። ኢሰፓ ከመምጣቱ በፊት በኢሰፓኮ ጊዜ ። እና የጊዜው መፈክርም "ኢሰፓአኮ ተልኮ ይሳካል !" የሚል ነበር ። ታድያ ቆምጬ አንድ ቀን ንግግር አድርገው ካበቁ በሁዋላ ተገቢውን መፈክር በማሰማት ህዝቡ እንዲበተን ያደርጋሉ ። ሁዋላ በማግስቱ ትዝ ሲላቸው ከመፈክሮቹ ሁሉ "የኢሰፓአኮ ተልኮ ይሳካል !" የምትለዋን ዘንግተዋታል ። ስለዚህ ቶሎ ብለው ህዝብ እንዲሰበሰብ ያደርጉና በሉ ግራ እጃችሁን ወደላይ ይላሉ ። ህዝቡ ግራ እጁን ይሰቅላል ። ታድያ በመሀል ያቺ መዘዘኛ በፈክር አሁንም ትጠፋለች ። ቢያስቡዋት ቢሉዋት ቢሰርዋት ትዝ አልላቸው አለች ። ይሄኔ ቆመው ተናደዱና እንዲህ የሚል መፈክር አሰሙ ይባላል ። "ሰሞኑን ከመጣው መፈክር ጋ ወደፊት !"
2. ቆምጬ የካቲት 66 ፖለቲካ ትምህርት ቤት ገብተው ለ6 ወራት የፖለቲካ ትምህርት ቀስመው ነበር ። ታድያ በዚያችው እውቀት ሲንቀሳቀሱ ከርመው ሳለ ለሎች ካድሬዎች ለተጨማሪ የፖለቲካ ትምህርት ወደ ጀርመን መሄዳቸውን ይሰማሉ ። እንዲያ ከሆነ ታድያ እሳቸው እናርጅ እናውጋ ውስት የሚቀመጡበት ምክንያት ምንድነው ? ባስቸኩዋይ ማመልከቻ ማስገባት ነበረባቸው ። ማመልከቻውን ታድያ እንዲህ ሲሉ ነው የጻፉት ይባላል ። ግዋድ ካሳዬ አራጋው የ ....ተጠሪ ። ከዚህ በፊት የካቲት 66 ገብቼ ለ6 ወራት የፖለቲካ ትምህርት መቅሰሜ ይታወቃል ። ስለሆነም በዚች ባገኘሁት ትምህርት ህብረተሰቡን ሳስተምር ቆይቼ ትምህርቱ አሁን ያለቀብኝ ስለሆነ ሌላ ተጨማሪ ትምህርት ከወደጀርመን አገኝ ዘንድ ወደዚያው እንዲልኩኝ እጠይቃለሁ ።
3. ጋዜጠኛው ፦ ጓድ ቆምጬ አምባው ኢምፔርያሊዝምን እንዴት ያዩታል ? ቆምጬ ፦ እናንተ እንዳሻችሁ እዩት እኔ ግን በጎሪጥ ነው እማየው (አሉ ይባላል)።
4. አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ቆምጬን ሊጎበኛቸው ብቅ ብሎ ኖሮ "እሺ ጓድ ቆምጬ አምባው አጠቃላይ እንቅስቃሴዎ ምን ይመስላል ?" በማለት ይጠይቃቸዋል ። ቆምጬም ሲመልሱ "...እንግዲህ በዚህ በኛ ወረዳ አብዮታዊው እንቅስቃሴ ጦፏል ። በኢኮኖሚው በኩል ገበሬው ቆላውን ሰንጎ ይዞታል ። በፖለቲካው በኩል ደሞ እነና ካድሬው ህዝቡን ሰንገን ይዘነዋል ።" አሉ ይባላል ።
5. ጋዜጠኛው ፣ “ለመሆኑ ማህበራችሁ ሴቶችን ያቅፋል ¿’’ ቆምጬም ሲመልሱ “ሲመሽ መች ይቀራል”