Jump to content

ሴም

ከውክፔዲያ
ሴም በ1546 ዓም እንደ ተሳለ

ሴም (ዕብራይስጥ፦ שֵׁם /ሸም/) በብሉይ ኪዳንና በአይሁድክርስቲያንእስላም ሥነ ጽሑፍ ዘንድ በኖኅ መርከብ ላይ ከማየ አይኅ ካመለጡት ከኖኅ ሦስት ወንድ ልጆች መሃል አንዱ ነው። ወንድሞቹ ካምያፌት ነበሩ፤ ልጆቹም ኤላምአሦርአራምአርፋክስድሉድ ናቸው።

መጽሐፈ ኩፋሌ ዘንድ ሴም በ1207 ዓ.ዓ. ተወለደ፤ በዚህ አቆጣጠር በ1308 ዓ.ዓ. ማየ አይኅ ወይም የጥፋት ውኃ በደረሰበት ዓመት የሴም ዕድሜ 101 ዓመት ያህል ነበር። ሚስቱም ሰደቀተልባብ ተብላ በመርከቡ ላይ ደግሞ አመለጠች። በስምምነት ሴም የተቀበለው የምድር ርስት ዕጣ በእስያ ከጢና ወንዝ (ዶን ወንዝ)ና ከግዮን ወንዝ (አባይ ወንዝ) መካከል ተገኘ። (ስለ ሴም ሚስት ስም በሌሎች ልማዶች ውስጥ፣ ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ ይዩ።)

ሴም፣ ካምና ያፌት በ1896 ዓም ስዕል

ኦሪት ዘፍጥረት 11:10 ዘንድ፣ ሴም 100 ዓመት ሲሆን ከጥፋት ውሃ 2 ዓመት በኋላ አርፋክስድን ወለደ፤ ከዚያ ሌላ 500 ዓመት ቆይቶ ባጠቃላይ 600 ዓመታት ኖረ። ይህ ከ2864 እስከ 2264 ዓመት ያህል ድረስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሊሆን ይችላል።

በልማድ ዘንድ ልጆቹ ኤላምአሦርአራምከለዳውያንልድያ የተባሉትን ጥንታዊ ብሔሮች ወለዱ። እስራኤልአረቦችአግዓዝያን ከከለዳውያን (አርፋክስድ) ዘር ወጡ። በቋንቋ ጥናት ኤላማውያን ወይም ልድያውያን የሴማዊ ቋንቋ ተናጋሪዎች አልነበሩም፤ የሴም ዘር ያልሆነው የከነዓን ሕዝብ ግን ሴማዊ ቋንቋ ተናገሩ፤ ዘመናዊ ዕብራይስጥም የከነዓንኛ አይነት ይመስላል።

በአንዳንድ የአይሁድ ምንጭ የመልከ ጼዴቅ መታወቂያ በውነት ሴም የኖህ ልጅ ነበረ። በሌሎች ጽሑፎች ውስጥ ግን መልከ ጼዴቅ የሴም ልጅ ልጅ ይባላል።

በእስልምና ሥነ ጽሑፍ ብዙ ጊዜ ሴም (አረብኛ፦ /ሳም/) እንደ ነቢይ ይቆጠራል።