Jump to content

መርኸፐሬ

ከውክፔዲያ

==

መርኸፐሬ
«መርኸፐሬ ሶበክሆተፕ» የሚል በጥንዚዛ
«መርኸፐሬ ሶበክሆተፕ» የሚል በጥንዚዛ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1646 ዓክልበ. ግ. ?
ቀዳሚ 7 ሶበክሆተፕ ?
ተከታይ ሰኸቀንሬ ?
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

==


መርኸፐሬላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1646 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።


ዘመኑ በሂክሶስ ጦርነት ዘመን ውስጥ እንደ ነበር ይመስላል። ከመርካውሬ 7 ሶበክሆተፕ ቀጥሎ እነማን በጤቤስ እንደ ገዙ ግልጽ አይደለም፤ ብዙ ስሞች ከቶሪኖ ቀኖና እንደ ጠፉ ይመስላል። ከሥነ ቅርስ የተረጋገጡት ግን መርኸፐሬ እና ሰኸቀንሬ ብቻ ናቸው። የመርኸፐሬ ተከታይ «መርካሬ» ነበር ሲል ሊነብብ ይችላል፤ ለርሱ ግን ምንም ማስረጃ ገና አልተገኘም። እነዚህ ነገሥታት ለረጅም ጊዜ እንደ ገዙ አይታስብም። በዚህም ሰዓት በአቢዶስ ዙሪያ አዲሱ የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነጻ እንደ ሆነ ይታስባል። የሚቀጠለው የጤቤስ ፈርዖን ሰኸምሬ ጀሁቲ16ኛው ሥርወ መንግሥት ጀማሪ ተብሏል።

ከቶሪኖ ዝርዝር በቀር፣ የመኸፐሬ ስም በሥነ ቅርስ የታወቀው ከአንድ ጥንዚዛ ምልክትና አንድ ሚዛን ክብደት ብቻ ነው።

ቀዳሚው
7 ሶበክሆተፕ ?
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1646 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰኸቀንሬ ?