Jump to content

ሐቲ

ከውክፔዲያ
(ከሃቲ የተዛወረ)
ሐትኛ የተናገረበት ሥፍራ (በሩስኛ)

ሐቲ በጥንታዊ አናቶሊያ የተገኘ ብሔር ነበረ። ዋና ከተማቸው ሐቱሳስ ነበር። ሐሊስ ወንዝ አገራቸውን ይዞር ነበር።

ሐቲ የሚለው ስም ከአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ዘመን ጀምሮ (2070 ዓክልበ. ግድም) ይታወቃል። የአካድና የአሦር ነጋዴዎች በሐቲ የራሳቸውን ሠፈሮች (ካሩም) ሲኖሯቸው የሳርጎንን እርዳታ ይጤይቁ ነበር፣ ሳርጎንም የቡሩሻንዳ ንጉሥ ኑርዳጋልን እንዳሸነፈው ይባላል። የሳርጎን ተከታይ ናራም-ሲን በሐቲ ንጉሥ ፓምባ ተዋጋ።

የሐቲ ሰዎች ቋንቋ ሐትኛ ዝምድናው የማይታወቅ ነው። በኋላ ዘመን ሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋ የተናገረ ሕዝብ ከካነሽ ተነሣ፣ ቋንቋቸውንም «ነሺሊ» (የካነሽ ቋንቋ) ይሉት ነበር። ግዛታቸውን በሐቲ ላይ ካስፋፉ በኋላ አገሩን «ሐቲ» በሚለው መጠሪያ ማለታቸውን አልተዉም። «ሐቲ» ከዕብራይስጥ ስም «ሔቲ» (ኬጢ) ጋር ተመሳሳይነት ስላለው እነዚህ ሰዎች አሁን በእንግሊዝኛ «ሂታይት» (ኬጥያውያን) ይባላሉ፣ ሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋቸውም («ነሺሊ») ኬጥኛ ይባላል። የቀደሙት የሐቲ ብሔር ግን በዘመናት ላይ ከኬጥያውያን ጋር ተቀላቀሉና ልዩ መታወቂያቸውን አጡ።